Dr. Elias Gebru
Our founder and CEO Dr. Elias Gebru (Asst. Prof.) is a certified psychotherapist and psychiatry specialist, author of five best-selling books (including “Aremimo”), Life Coach, Hypnotherapist, Art Therapist, Certified Energy Healer & Crystal Healer, Personal Development Coach, Corporate Leadership and Team Excellence Trainer, social media marketing expert, charity worker & event organizer.
CEO of Aremimo
Certified psychotherapist
Specializing in psychiatry
Author of five books
Hypnotherapist
Certified Emotional Intelligence & Personal Development Coach
Social media marketing
Life Coach
Here are a few examples of reader responses to the book so far:
“
መጋቢ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ
መጋቢ ሀዲስ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ
በአንድሮሜዳ የቴሌቭዥን መርሐ ግብር ላይ በመቅረብ ሰፊ ኢትዮጵያዊ ዕውቀትን ያጋራን Dr. Elias GebruAremimo አርምሞ በሚል ዐዲስ የምርምር፣ የፍቅር፣ የሃይማኖት ይዘት ባለው የልብ ወለድ መጽሐፍ ብቅ ብሏል።
የግእዝ ቋንቋ ሊቅ አለቃ ኪዳነ ወልድ "አርምሞ" የሚለውን ሲፈቱት መርመም፤ ዝም ጸጥ ጫ ማለት አፍን ከንፈርን መግጠም መዝጋት፣ ከሁከት ከነገር ማረፍ፣ ዕረፍት፣ ህድአት ይሉታል።
ፈላስፋውም "ተናግሮ ብሩር ውእቱ አርምሞሰ ወርቅ ይእቲ" (መናገር ብር ነው። ዝምታ ግን ወርቅ ናት) ይላል። ከሚጮህና ኪስን ልቅደድ ከሚል አነስተኛ ዋጋ ካለው ከሚንኳኳ ሳንቲም ይልቅ ድምፅ የማያሰማው ብር ዋጋው ከፍ ያለ ነው። ድምፅ የሚያሰማውና የሚንቦጫቦጨው ትንሽ የውሃ መጠን የያዘ ያልሞላ እንስራ ሲኾን፤ ድምፅ የማያሰማው እንስራ በአግባቡ የውሃ መጠን ይዞ የሞላው ነው።
በሥጋ፣ በነፍስ፣ በመንፈስ የተዋቀረው የሰው ልጅ የውስጥ ውስጥ የኾነው መንፈሱ ታላቅ የምስጢር ቋት እንደኾነ፤ ከአእምሮ ጠባይዕ ይልቅ አእምሮ መንፈሳዊው መዝገበ ምስጢር እንደኾነ ኹሉ ውስጡ በአርምሞ የታከመ ውጪውም ጤናማ ነው። ውሳጣዊ ልቡ የተረጋጋ ከልቡ መዝገብ ቃላትን ወልዶ ቢናገር እንኳ አንደበቱ እንደ እሳት ወላፈን አይፋጅም፣ የሰው ዐጥንት በስድብ ቃል አይሰብርም። ይልቁኑ ፈዋሽ፣ ጠጋኝ፣ የሚያረጋጋ ይኾናል በባሕር ውስጥ ማዕበል የተነሣባት ጀልባ ለመኼድ እንድትቸገር ውስጡ የታወከበትም፣ አርምሞን ያልያዘ በእግረ ኅሊና ለመኼድ፣ እደ ኅሊናውን ለመዘርጋት፣ በዕዝነ ልቡና ለመስማት፣ በአብራከ ልቡና ለማንበርከክ ያዳግተዋል። በአጠቃላይ ተመስጧዊ ሕይወት የራቀውና አእምሮ መንፈሳዊን ገንዘብ ማድረግ ያዳግተዋል።
በመኾኑም አርምሞ መጽሐፍ ማንበብ ለስክነት በእጅጉ ይጠቅማልና የዶክተር ኤልያስን መጽሐፍ እናንብብ እያልኩ ለአርምሞ መጽሐፍኽ እንኳን ደስ ያለህ እላለው።
“
ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ ጂግሳ
ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ አእምሮ፥ እንደ ሩሲያዊው ደራሲ አንቷን ቼኮቭ በሙያው ሀኪም ነው። ሆኖም ለስነጽሁፍ ባለው ፍቅር ጊዜውን አጣቦ እየፃፈ ይህን ልብወለድ ታሪክና ሁለት ሌሎች መጻህፍትን በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ ከእዚህ ቀደም አስነብቦናል።
ይህ መጽሀፍ የማይነኩና የማይደፈሩ ጥልቅ መንፈሳዊ ጉዳይዎችን ያዘለ ነው። አእምሮው በሳይንስ ከተቀረጸ ምሁር ከሳይንስ ተጻራሪ የሆነ ይዘትን ማውጠንጠኑ ብዙም ያልተለመደ ነገር ነው።
የኢትዮጵን የልጅነት ስም ኢትኤልን ለዋናው ባለታሪክ ሰጥቶ እና ሌሎች ከእሱ ጋር የሚጓዙ ጽዮን፣ አብርሃም፣ መርየም፣ ቶላ፣ ናዖድ፣ ቢታንያ፣ ዘይኔና ዮሴፍ የተሰኙ ባህርያትን ፈጥሮ ታሪኩን በህክምና ትምህርት በተሰማሩ ተማሪዋች መሀል አሰናስሎ ጀምሮ እንደ ፕ/ር እሴና ዶ/ር ሳሙኤል ባሉ ምሁሮች አጅቦ እስከ አስገራሚዎቹ ባህታዊ፣ ወልዮችና አባ-ገዳዎች ድረስ አዋዝቶ ያዳርሰዋል።
ደራሲው ከሚያነሳቸው ርእሶች ውስጥ ዛሬ የኢትዮጵያን ኀብረትሰብ የተበተበው የጥንቆላ አስከፊነት አንዱን ስፍራ ይዟል። በተጨማሪም ገናናውን የኢትዮጵያ ታሪክና የ<ቶ> ጥበብን ይዳስሳል። ከእዚህ ሁሉ በላይ በጠቅላላው የኢትዮጵያዊ ሙስሊሞች እና ክርስትያኖች ጥንታዊ ግንኙነትና ወዳጅነት፥ እንዲሁም በእስልምና እና ክርስትና ሀይማኖቶች መሀል የአሉትን ተመሳሳይነት፥ አንድነት እና ኀብረት አጉልቶ ያንጸባርቃል።
ታሪኩም ምስጢራዊ እና መንፈሳዊ ሆኖ፥ እያጓጓ እና እየተሽቆለቆለ ይፈስሳል። ቃላቱና አ/ነገሮቹም በቦታቸው ገብተው እርስበርሳቸው ተዋህደዋል። ይህን መጽሀፍ ሁሉም ሰው ቢያነበው የፈንጠዝያው(inspiration)ን እና የአእምሮውን አድማስ ያሰፋል ብዬ አስባለሁ።
“
ሳምሶን ከበደ
ይህ መፅሐፍ በጣም ጥልቅ የሆነ በጥንት ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ጠቢባን ወቅዱሳን፤ የመንፈሳዊ፣የሥነ ምግባር ፣የሐገር በቀል እውቀቶች ምርምር፣ የታሪክ ምርምር ታላቅ ስብእና፣የተቋረጠውን በጥበብ ብሎም በማስተዋል የተመሠረተውን የጥንቱንና ያሁኑን ትውልድ በፍቅርና በአንድነት የሚያሰባስብ፣ የሚያስተሳስር ለዛና ውበት ያለው የሥነ-ፅሁፍ ሥራ ነው፡፡በማስተዋል መንፈስ ታነቡት ዘንድም "በኤቶዮጵ"አምላክ ስም ጀባ ብለናቹሃል!!!! መልካም ንባብ
የጥንታዊው የጠልሰም ስዕል ጠበብት
“
ናዝራዊው ሄኖክ
"ኤቶዮጵ "የቃልኪዳኗን ምድር በታሪክ ከዘፍጥረት፣ ከአዳም እትብት ፤ ጥበብ ማዶ እስከ ሄኖክ ፤ ገፍቶ ዘልቆ መልከፀዴቅ የአስራት ልጁን አብርሃምን ፣ የኔታውን ዮቶር-አብን ነፃ አውጭውን ደቀ-መዝሙር ሙሴን! ብዙ ብዙ ብዙ... ብሎ እልፉን ዳሶ.. ከአክሱም አናት እስከ ኦዳ አባ ገዳ ። መንፈሳዊ ጥልቁን ሰመጥሶ ሰርጦ #ቶ አህዶ ያሳየናል።
" መሪራስ ቢሞት ኤልያስ ተተካ- ዶሴ አገላባጭ ብቻ ለብቻ!!!"
ከደብረ-ማርቆስ ጎዣም
“
ፍሬገነት
ይህን መጽሐፍ ካነበብኩኝ በኋላ ታሪኮቹ በጣም ወደ ውስጤ ከመስረጻቸው የተነሳ አንዳንዶቹ ገጸ-ባህሪያት በህልሜ ጭምር ይመጡብኝ ነበር፡፡
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ
“
ተማሪ ሰናይት ከድር
ኤቶዮጵን አንቡብና እንደኔ ወደ ራሳችሁ ተመለሱ፣ ቀልባችሁን ሰብስቡ፡፡
ከሽሬ - ትግራይ
“
ኃይለመለኮት_አሰፋ
ይህ ወጣት ደራሲ በዚህ ስራው ከአንጋፋ ደራሲያን ተርታ ሊመደብ ይችላል! ብሔሮች እና ሀይማኖቶች ሀገራችን ላይ በተናጠል ክር ናቸው፤ ያውም ባለ ብዙ ቀለማት! አሳምሮ ገማጅ ሲገኝ በህብረ ቀለማት ስብጥር የተቆጠቆጠ ገመድ ይፈጠራል! እነሆ ወጣቱ ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ አዕምሮ እስልምናን ከክርስትና፣ ብሔርን ከብሔር፣ ልብን ከልብ ገምዷል!
መምህርና የቀድሞ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ም/ዋና አዘጋጅ

